Month December 2023

በትውልድ መካከል የሚካሄድ የፖለቲካ ውይይት ጠቀሜታ፣ አስፈላጊነት እና በጎ ተፅዕኖ ላይ ያተኮረ የኤክስፐርቶች ማረጋገጫ ዐውደ ጥናት ተከናወነ

ትምራን ያዘጋጀችው በትውልድ መካከል የሚካሄድ የፖለቲካ ውይይት ጠቀሜታ፣ አስፈላጊነት እና በጎ ተፅዕኖ ላይ ያተኮረ የኤክስፐርቶች ማረጋገጫ ዐውደ ጥናት መድረክ ታኅሣሥ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተከናወነ። ዐውደ ጥናቱ የተከናወነው ሦስት ሳምንት ገደማ በፊት በተደረገው ውይይት ላይ በተቋቋመው የተግባር ኮሚቴ…

በፕሮፖዛል ዝግጅት እና ፕሮጀክት አተገባበር ላይ ለትምራን ባለሞያዎች ለሦስት ቀናት የተዘጋጀው ሥልጠና ተጠናቀቀ

በፕሮፖዛል ዝግጅት እና ፕሮጀክት አተገባበር ላይ ለትምራን ባለሞያዎች ከታኅሣሥ 08-10 ቀን 2016 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ የተዘጋጀው የአቅም ግንባታሥልጠና ተጠናቀቀ። በሥልጠናው የመጀመሪያ ቀን በፕሮጀክት አተገባበር እና ልምድ ረገድ በትምራን ባለሞያዎች ዘንድ ያሉ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ የፕሮጀክት አስፈላጊነት፣ ምንነት፣ ለምን ያስፈልገናል፣ አስተዳደር፣…

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል። ምክር ቤቱ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ በውሳኔ ቁጥር 02/2016 ሆኖ አጽድቋል።…

ለጥምረት የሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ጽ/ቤት ባለሞያዎች ለሁለት ቀናት የተሰጠው ሥልጠና ተጠናቀቀ

ለጥምረት የሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ጽ/ቤት ባለሞያዎች ታኅሣሥ 03 እና 04 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ የተሰባሰቡ መረጃዎችን ማደራጀት እና መተንተን የተመለከተ ሥልጠና ተጠናቀቀ። ሥልጠናው ኢንክሉሲቭ ፒስ በተሰኘ መንግሥታዊ ያልኾነ ድርጅት የተሰጠ ሲኾን፣ በመጀመሪያው ቀን የሰላም ሂደት…

“ትምራን-ሴቶች በሰላም አመራርነት ውስጥ ያላቸው ሚና” በሚል ጭብጥ የተካሄደው የሥዕል ዐውደ ርእይ መድረክ ተጠናቀቀ

“ትምራን-ሴቶች በሰላም አመራርነት ውስጥ ያላቸው ሚና” በሚል ጭብጥ ከታኅሣሥ 01-02 ቀን 2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል የተካሄደው የሥዕል ዐውደ ርእይ መድረክ ተጠናቀቀ። ለሁለት ቀናት የቆየውን የሥዕል ዐውደ ርእይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የጎበኙት ሲኾን፣ ተጋባዥ አምባሳደሮች፣ ለጋሽ ድርጅቶች፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ…

ትምራን-ሴቶች በሰላም አመራርነት ውስጥ ያላቸውን ሚና የሚያሳይ የሥዕል ዐውደ ርእይ# በሥዕል

ታኅሣሥ 01 ቀን 2016 ዓ.ም የተከፈተው ትምራን-ሴቶች በሰላም አመራርነት ውስጥ ያላቸውን ሚና የሚያሳይ የሥዕል ዐውደ ርእይ ታኅሣሥ 02 ቀን 2016 ዓ.ም ሙሉ ቀን የሚቆይ ሲኾን፣ እስከ ምሳ ሰዓት ድረስ ለማንኛውም ጎብኚ ክፍት ነው። ከሰዓት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሴቶች በሰላም…