Month March 2024

ትምራን በተለያዩ ውትወታ እና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ስታከብር የቆየችውን የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል አጠናቀቀች

ትምራን ሴቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲኾኑ እና በሀገሪቱ ውሳኔ ሰጭነት ውስጥ ተገቢ ውክልና እንዲኖራቸው የማስቻል ራእይ በመሰነቅ መጋቢት 2012 ዓ.ም ከኢፌዴሪ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን የምዝገባ ምስክር ወረቀት በማግኘት ሥራ ከጀመረች አራት ዓመታት ተቆጥረዋል። መጋቢት ዓለም አቀፍ የሴቶች…

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለሴቶች አዎንታዊ እርምጃ እና የኮታ ሥርዓት መኖር አስፈላጊነት

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለሴቶች አዎንታዊ እርምጃ እና የኮታ ሥርዓት መኖር የሥርዓተ-ጾታ አድልኦን ለመቅረፍ እና ሴቶች በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ጉልህ ተነሣሽነት ነው። ኮታዎች በሕግ አውጭ አካላት ውስጥ ለሴቶች የተከለሉ መቀመጫዎች ዝቅተኛ ገደብ ወይም መቶኛ እንዲኖር እድል…

በፖለቲካ ተግባቦት እና የምርጫ ቅስቀሳ ክሂሎት ላይ ለትምራን ባለሞያዎች የተዘጋጀው የአሠልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ

የጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር የሲቪል ፒስ ሰርቪስ ከትምራን ጋር በመተባበር በፖለቲካ ተግባቦት እና የምርጫ ቅስቀሳ ክሂሎት ላይ ከመጋቢት 09-13 ቀን 2016 ዓ.ም ለትምራን ባለሞያዎች ያዘጋጀው የአሠልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ። በሥልጠናው ላይ የፖለቲካ ተግባቦት ምንነት፣ ተዋናዮች እና መገለጫዎች፣ በምርጫ ሂደት ውስጥ የፖለቲካ…

የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም መገንባት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው

የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም መገንባት የኢኮኖሚ አንድምታ አለው፤ የሰብአዊ መብቶችም ጉዳይ ነው። የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ የኾነበት ምክንያት ዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ሥርዓቶች የጾታ እኩልነትን የሚያበረታቱ በመኾናቸው ነው። በተመሳሳይ መልኩ የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም መገንባት የፋይናንስ ሀብቶች እነዚኽን ችግሮች መወጣት እንዲችሉ እና…

ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ በኦሮሚያ ክልል ያካሄዳቸው የአቅም ግንባታ ሥልጠና መድረኮች ማጠቃለያ መርሐ ግብር አካሄደ ከምሥራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለም እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ምድብ ለመጡ ሴቶች ሥልጠና ተሰጥቷል

ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ በኦሮሚያ ክልል ያካሄዳቸው የአቅም ግንባታ ሥልጠና መድረኮች ማጠቃለያ መርሐ ግብር መጋቢት 04 ቀን 2016 ዓ.ም በአዳማ ከተማ አካሄደ። ከማጠቃለያው መርሐ ግብር አስቀድሞ የክልሉ ሰባተኛ ምድብ የኾነው ከምሥራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለም እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ምድብ…