Admin

Admin

ትምራን ለመካከለኛ አመራር ሴቶች ለሦስት ቀናት ስትሰጥ የቆየችው ሥልጠና ተጠናቀቀ

ሥልጠናው ‘ሴቶች ለሰላም ግንባታ እና ውትወታ’ በሚል ጭብጥ ከሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል። ግንቦት 02 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የሦስተኛ ቀን ውሎ የሰላም ግንባታ ምንነት፣ አተገባበር፣ ተዋናዮች እንዲኹም ለሰላም ግንባታ የሚኾኑ የውትወታ ስልቶች ጋር የተያያዙ ሐሳቦች ላይ…

ትምራን ለመካከለኛ ሴት አመራሮች ያዘጋጀችው የሰላም ግንባታ እና ውትወታ ሥልጠና ኹለተኛ ቀን ውሎ ቀጥሏል

በሥልጠናው መጀመሪያ ቀን ውሎ ከተነሡ ጉዳዮች መካከል አራቱ የሴቶች የሰላም እና ደኅንነት አጀንዳዎች ማለትም መከላከል፣ ጥበቃ፣ ተሳትፎ እና መልሶ ግንባታ ባለድርሻ አካላት ላይ ከተሳታፊዎች በተነሡ ሐሳቦች ተጀምሯል። የሴቶች ሰላም እና ደኅንነት አጀንዳዎች ባለድርሻ አካላት ከኾኑት መካከል ቤተሰብ፣ ማኅበረሰብ፣ የትምህርት ተቋማት፣…

ትምራን ሴቶች ለሰላም ግንባታ እና ውትወታ በሚል ጭብጥ ለመካከለኛ አመራር ሴቶች ሥልጠና መስጠት ጀመረች

ትምራን ሴቶች ለሰላም ግንባታ እና ውትወታ በሚል ጭብጥ ለመካከለኛ አመራር ሴቶች ያዘጋጀችው ለሦስት ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ተጀመረ። ሥልጠናውን በንግግር የከፈቱት የትምራን ሥራ አስኪያጅ ኢየሩሳሌም ሶሎሞን፣ ትምራን ሴቶች ወደ ፖለቲካ አመራር እና ውሳኔ ሰጭነት…

የሴቶች አጀንዳዎችን ለሀገራዊ ውይይት ግብአት እንዲኾኑ ማጠናቀር ጠቃሚ ነው

ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ከሰባት ክልሎች እና ኹለት ከተማ አስተዳደሮች ያሰባሰባቸውን የሴቶች አጀንዳዎች አጠናክሮ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቅረብ ሚያዚያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ምክክር ማካሄዱ ይታወሳል። ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰቡትን የሴቶች አጀንዳዎች በማጠናቀር በምክክር ሂደቱ ውስጥ ማካተት…

ከዘጠኝ ክልሎች የተሰባሰቡ የሴቶችን አጀንዳዎች አጠናቅሮ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቅረብ የተዘጋጀው የመክፈቻ ምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ከሰባት ክልሎች እና ኹለት ከተማ አስተዳደሮች ያሰባሰባቸውን የሴቶች አጀንዳዎች አጠናቅሮ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቅረብ ሚያዚያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ያካሄደው የመክፈቻ ምክክር መድረክ ተጠናቀቀ። ለመድረኩ ተሳታፊዎች የእንኳን ደኅና መጣችኹ መልእክት ያስተላለፉት የጥምረቱ…