ጠበቃ መሠረት አያሌው የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

ጠበቃ ተስፋዬ ደረሰ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነዋል
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበርን ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በአመራርነት ለማገልገል ዛሬ ታኅሣሥ 04 ቀን 2018 ዓ.ም በግራንድ ኤልያና ሆቴል በተካሄደ የምርጫ ሥነ ሥርዓት ጠበቃ መሠረት አያሌው ማኅበሩን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።
በተመሳሳይ ማበኅበሩን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የሚያገለግሉ አባላት ለመሰየም በተካሄደው ምርጫ ጠበቃ ጀሚላ ክብረት እና ጠበቃ ቤዛ ንጉሤ ሴት ተወካዮች ሆነው ተመርጠዋል።


ትምራን ለሦስቱ ሴት ጠበቆች እንዲሁም ማኅበሩን በአመራርነት ለማገልገል ለተመረጡት ጠበቆች በሙሉ የተሳካ የሓላፊነት ጊዜ እንዲሆንላቸው ትመኛለች።

Share this post on