ትምራን ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ሴት ባለሞያዎች እና ሴታዊት ጋር የመልእክት ማጥራት ምክክር አካሄደች

ትምራን ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ሴት ባለሞያዎች እና ሴታዊት ጋር በመሆን ሴቶች በሀገራዊ ምክክር መድረክ ላይ ስለሚኖራቸው ሚና በተመለከተ የመልእክት ማጥራት ምክክር መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም በሐርመኒ ሆቴል አካሄደች።

የመልእክት ማጥራት ምክክሩ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ የመጣ ነው።

በምክክሩ ላይ ተለይተው የተጣሩት መልእክቶች ሴቶች በብሔራዊ ምክክሩ ላይ  ሊኖራቸው ስለሚገባው ሚና እንደ ሚዲያው ዓይነት ተቀርፀው ይሰራጫሉ።

ትምራን፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ሴት ባለሞያዎች እና ሴታዊት በሀገራዊ ምክክር መድረክ ሂደት ውስጥ ሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል በ50 የሲቪክ ማኅበራት የተመሠረተው ጥምረት ለሴቶች በሀገራዊ ምክር መድረክ አባል ናቸው።

Share this post on

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *