ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሲያከናውናቸው የቆዩ የሴቶች አቅም ግንባታ መድረኮች ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተከናወነ

ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ያዘጋጃቸው የአቅም ግንባታ መድረኮች ማጠቃለያ መርሐ ግብር ነሐሴ 01 ቀን 2016 ዓ.ም በሆሣዕና ከተማ ተከናወነ።

የማጠቃለያ መርሐ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ አማካሪ ወ/ሮ መንደሪን ጌታሁን፣ ሀገራዊ ምክክር በየደረጃው ሲደረግ ሴቶች አጀንዳቸውን እንዲቀርጹ፣ በሀገር ጉዳይ ላይ ደግሞ እኩል የሚወስኑ፣ የሚሳተፉ ብሎም የሚጠቀሙ ለማድረግ  ጥምረቱ ላከናወነው ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

የጥምረቱ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አስቻለው ማቴዎስ በበኩላቸው፣ ጥምረት ከፍሬደሪክ ኤቨርት ስቲፍተንግ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ማኅበር ጋር በመተባበር ያዘጋጃቸው መድረኮች በተናበበ ሁኔታ እንዲጠናቀቁ ድጋፍ ላደረጉ አካላት በሙሉ ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ የዕለቱ ተሳታፊዎች በቡድን ተከፋፍለው ክልላዊ አጀንዳ በመቅረፅ ካቀረቡ በኋላ በየምድቦች የተነሡ የሴቶች አጀንዳዎች ላይ ሐሳብ ሰጥተዋል።   

በመጨረሻም የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ማኅበር ሰብሳቢ ፎዚያ መሐመድ፣ የሴቶች አጀንዳ በአግባቡ እንዲቀረፁ እና ድምፃቸው እንዲሰማ ጥምረቱ ላደረገው ጥረት አመስግነው፣ የተነሡ አጀንዳዎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ሁሉም በየደረጃው ክትትል እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።  

ጥምረቱ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የመክፈቻ መድረክ ያካሄደ ሲሆን፣ ቀጥሎም ከሀዲያ፣ ጉራጌ እና ቀቤና፣ ምሥራቅ ጉራጌ እና ማረቆ፣ ስልጤ እና የም፣ ሀላባ እንዲሁም ከምባታ እና ጠምባሮ ለተውጣጡ ቁጥራቸው 300 በላይ ለሆኑ ሴቶች ተከታታይ ስድስት መድረኮችን አከናውኗል።

The Coalition for Women’s Voice concluded CER women capacity building forums

The Coalition for Women’s Voice in the National Dialogue concluded CER women capacity building forums that aimed women active participation in the national dialogue process on August 07, 2024 G.C at Hosaena town.

Mrs. Menderin Getahun, CER Women and Social Affairs Bureau Head Advisor, in her opening remark thanked the Coalition for organizing cluster based consultations to support the regional women to coin their agendas, to participate and decide equally on the fate of the country, and share from any benefit though.   

The Coalition project Coordinator, Mr. Aschalew Mathewos, pointed with the support of FES-Ethiopia the Coalition organized CER women consultations in collaboration with the regional Women’s Association; and extended his gratitude to all stakeholders participated in the process to conclude the events successfully.

Then the participants grouped, coined women’s agendas and presented for the mass as well as all CER cluster agendas deliberated to them and forwarded their recommendations on them.

At the end, CER Women’s Association Chairwoman, Foziya Mohammed, also thanked the Coalition for helping CER women to coin their agendas and for giving an opportunity their voices to be heard. She noted to make women’s agendas bear fruit all stakeholders should follow earnestly.    

 On July 30, 2024 G.C, the Coalition started with CER officials opening session and then conducted six consecutive cluster consultations including Hadiya, Gurage and Qebena, East Gurage and Mareqo, Silte and Yem, Halaba as well as Kembata and Tembaro having more than 300 woman participants.

Share this post on