JUSTICE FOR BABY HEAVEN!

ትምራን ሔቨን የተባለች የ7 ዓመት ሕፃን በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ ለሞት መዳረጓን ወላጅ እናቷ በኢዮሃ ሚዲያ ቀርባ ከሰጠችው ቃለ ምልልስ ተገንዝባለች። በቃለ ምልልሱ ላይ ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብ የ25 ዓመታት እስር ቢፈረድበትም፣ ተባባሪዎቹ በወላጅ እናቷ ላይ ማስፈራሪያ እያደረሱባት ብሎም ፍርድ ለማስለወጥ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ተመልክታለች። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢ እየሆኑ በመምጣታቸው በሁሉም አካባቢ በሕግ የተደነገጉ ቅጣቶች ወጥነት ባለው መልኩ እንዲተገበሩ በአጽንኦት ትጠይቃለች።

ፍትሕ ለሔቨን! ፍትሕ ለወላጅ እናቷ! ፍትሕ ለተጠቂ እናቶች እና ሕፃናት!

Share this post on