Barriers for women in politics

Women face several barriers in politics, including:

  1. Gender Stereotypes and Cultural Norms: Societal expectations often prioritize men as leaders, discouraging women from pursuing political careers.
  2. Lack of Access to Resources: Women frequently have limited access to campaign funding, networks, and media exposure.
  3. Violence and Intimidation: Women politicians often face threats, harassment, and violence aimed at discouraging their participation.
  4. Unequal Family and Social Responsibilities: Women typically bear a disproportionate share of household and caregiving duties, limiting their political engagement.
  5. Structural and Institutional Barriers: Discriminatory electoral systems, lack of gender quotas, and biased political institutions hinder women’s representation.
  6. Limited Political Mentorship and Role Models: Fewer women in leadership roles reduce mentorship opportunities and discourage new entrants.
  7. Legal and Policy Barriers: Absence of supportive legal frameworks or protective measures can impede women’s political participation.

ሴቶች በፖለቲካ ውስጥ እንዳይሳተፉ የሚያጋጥሙ መሰናክሎች

ሴቶች በፖለቲካ ውስጥ እንዳይሳተፉ በርካታ መሰናክሎች ይገጥማቸዋል። ከእነዚህም መካከል:-

  1. የሥርዓተ ጾታ መድልኦዎች እና የባሕል ገደቦች:-ብዙውን ጊዜ ኅብረተሰቡ ሴቶች ወደ ፖለቲካ እንዳይመጡ በመገደብ ወንዶች መሪነቱን እንዲይዙ ቅድሚያ ይሰጣል።      
  2. የሀብት ምንጮችን ማግኘት አለመቻል:-በተደጋጋሚ ጊዜ ሴቶች ለምርጫ ቅስቀሳ፣ ትስስር ለመፍጠር እና ወደ ሚዲያ ለመውጣት የገንዘብ ችግር ሲገጥማቸው ይታያል።
  3. ሁከት እና ማስፈራራት:-ብዙ ጊዜ ሴት ፖለቲከኞች ተሳትፎአቸውን ለመግታት ማስፈራራቶች፣ ትንኮሳ እና ብጥብጥ ይፈጸምባቸዋል።
  4. ፍትሐዊ ያልሆነ የቤተሰብ እና ኅብረተሰብ ሓላፊነቶች:-ሴቶች በቤት ውስጥ እና በእንክብካቤ ተግባራት ውስጥ እኩል ያልሆነ ሓላፊነት ይጫንባቸዋል፤ ይህም የፖለቲካ ተሳትፎአቸው የተገታ እንዲሆን ያደርጋል።  
  5. መዋቅራዊ እና ተቋማዊ መሰናክሎች:-አግላይ የምርጫ ሥርዓቶች፣ የሥርዓተ ጾታ ኮታ አለመኖር እና አድሏዊ የፖለቲካ ተቋማት መኖር የሴቶችን የፖለቲካ ውክልና ከሚገድቡ መካከል ይጠቀሳሉ።
  6. ሴቶችን ለፖለቲካ የማብቃት ውስን ተግባራት እና አርአያ የማግኘት ችግር:-በአመራርነት ላይ የሚገኙ ሴቶች ቁጥር ማነስ በፖለቲካ ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን የማብቃት ሥራ የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ አዳዲስ ሴት ፖለቲከኞች ወደፊት እንዳይመጡ ምክንያት ይሆናል።
  7. የሕግ እና የፖሊሲ ገደቦች:- ደጋፊ የሕግ ማእቀፎች አለመኖር አልያም ገዳቢ እርምጃዎች መኖር የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ከሚቀንሱ ምክንያቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

#TIMRAN@5 #Womenpolitics #WomenLeadership #WomenPeaceandSecurity

Share this post on