The Coalition conducted the 2nd round Women’s Agendas consolidation session

The Coalition for Women’s Voice in the ND conducted the 2nd round Women’s Agendas consolidation session collected from Central Ethiopia, Gambella & Amhara regions.

The agendas will be submitted to the ENDC & an advocacy activity will follow to get focus on the national plenary.


ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ከሥራ አስፈጻሚ እና ከሥራ ቡድን አባላት ድርጅቶች የተውጣጡ ተሳታፊዎች እንዲሁም ከትምራን ጽ/ቤት የመጡ ባለሞያዎች በተገኙበት ሁለተኛ ዙር የሴቶች አጀንዳዎችን የማደራጀት ተግባር አከናወነ።


በዋናነት ከማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ እና አማራ ክልሎች የተሰበሰቡትን ጨምሮ በማኅበረሰብ አቀፍ ውይይት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ሲዳማ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተሰበሰቡ ተጨማሪ የሴቶች አጀንዳዎች ተደራጅተዋል።


መርሐ ግብሩ ከመስከረም 26-29 ቀን 2018 ዓ.ም ለአራት ቀናት በቢሾፍቱ ከተማ ተከናውኗል።


የተደራጁት የሴቶች አጀንዳዎች ላይ የማረጋገጥ እና የአርትኦት ሥራ ተሠርቶ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይቀርባሉ፤ በቀጣይነትም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚከናወን ምክክር ወቅት ትኩረት እንዲሰጣቸው ለማድረግ የሚያስችሉ የውትወታ ሥራዎች ይካሄዳል።


ጥምረቱ ሐምሌ 2016 ዓ.ም ውስጥ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ ከዐሥር ክልሎች የተሰባሰቡ የሴቶች አጀንዳዎችን ማስረከቡ ይታወሳል።

Share this post on