ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል።

ምክር ቤቱ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ በውሳኔ ቁጥር 02/2016 ሆኖ አጽድቋል።

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የጽ/ቤት ሓላፊ ሆነው አገልግለዋል።

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን በሰብሳቢነት እንዲመሩ በመመረጣቸው ትምራን እንኳን ደስ አለዎት ማለት ትፈልጋለች።

Share this post on

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *