“በኢትዮጵያ የሴት መሪዎች ኹኔታ” በሚል ጭብጥ በተደረገ ጥናት ላይ የማረጋገጫ ዐውደ ጥናት ተካሄደ

የማረጋገጫ ዐውደ ጥናቱን ትምራን ከተመድ የሴቶች ልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲኾን፣ የተለያዩ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ተወካዮች፣ የክልል ቢሮዎች ተወካዮች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወካዮች እንዲኹም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በተገኙበት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሂዷል።

ጥናቱ በፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ በክልል ቢሮዎች፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት እና በክልል ምክር ቤቶች ምን ያኽል የሴት አመራሮች እንዳሉ የሚያሳይ ነው፤ የማረጋገጫ ዐውደ ጥናቱ በጥናቱ ዙርያ ከተጋባዥ ተሳታፊዎች ገንቢ ሐሳቦች የተሰበሰቡበት መድረክ ነበር።

በኢትዮጵያ የተመድ የሴቶች ልማት ፕሮግራም ልዩ ባለሞያ ወ/ሮ ደሴት አበበ እንደዚኽ ዓይነት ጥናቶች በአንድ ተቋም ብቻ ከሚሠሩ ይልቅ የሴቶች መብት ላይ የሚሠሩ ተቋማት በጥምረት ቢሠሩ የተሻለ እንደሚኾን እና ዐውደ ጥናቱን የታደሙት ተቋማትም መረጃ በመስጠት የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የራሳቸውን ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ገልጸዋል።

Share this post on

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *