info@timran.et | +251 116 73 48 48
የትምራን ጊዜያዊ ሥራ አስፈጻሚ በሲቪክ ማኅበራት ብሔራዊ የጥናት ጉባኤ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቀረቡ

የትምራን ጊዜያዊ ሥራ አስፈጻሚ ማኅደር ዳዲ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሲቪክ ማኅበራት ብሔራዊ የጥናት ጉባኤ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቀረቡ።
ጥናቱ ትምራን ሴቷ ሰላምን ትምራ በሚል ፕሮጀክት በስምንት ክልሎች ማለትም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ በቀድሞው ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች እንዲኹም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያከናወነቻቸው የሴቶች የሰላም መድረኮች ላይ የተነሡ ሐሳቦችን መሠረት ያደረገ ነው።
በመድረኩ ላይ በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ የሲቪክ ማኅበራት ሚና የተመለከቱ በርካታ ጉዳዮች ቀርበዋል።
ኅዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም የተከፈተው የጥናት ጉባኤ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ስካይላት ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል።