ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ እንኳን ደስ አለኽ!

የትምራን ቦርድ ጸሐፊ የኾነው እና የሰዎችን ታሪክ በመሰነድ የሚታወቀው ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ ባለፉት ሰባት ዓመታት የ45 ሰዎችን ታሪክ በሲዲ፣ የ16 ሰዎችን የሕይወት ታሪክ በመጽሐፍ አዘጋጅቶ አውጥቷል።

የ180 የሚዲያ ሰዎችን ታሪክ የያዘ ባለ 600 ገጽ የመጀመሪያ ቅጽ የአማርኛ መዝገበ አእምሮ በማዘጋጀት አሳትሟል።

ይኽንን መሠረት በማድረግ መቀመጫውን አሜሪካን ሀገር፣ ዳላስ፣ ቴክሳስ ያደረገው ዓድዋ የታሪክ እና የባሕል ኅብረት በግለ ታሪክ ዘርፍ ሠኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም የልዩ ምሥጋና እውቅና ስለሰጠው ትምራን እንኳን ደስ አለኽ ትላለች።

Share this post on

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *