Updates

Updates

The safety of vulnerable women is an immediate ethical and structural demand of the WPS agenda

የሴቶች ሰላም እና ደኅንነት አጀንዳ አንገብጋቢ ከሆኑ ፍላጎቶች አንዱ ተፈናቃይ እና ‘የተረሱ’ እናቶችን ጨምሮ፣ ተጋላጭ የሆኑ ሴቶችን ደኅንነት ማረጋገጥ ነው። የሴቶች፣ ሰላም እና ደኅንነት (WPS) ረቂቅ ብሔራዊ የድርጊት መርሐ-ግብር በወሲባዊ ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ጥበቃ ላይ ያተኮሩ ግልጽ የሆኑ የሥራ መመሪያዎችንና የተመደበ በጀት ማካተቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። የዜጎችን የሰውነት ክብርን ለመጠበቅ እና መረጋጋትን ለማስፈን የሰላም እና ደኅንነት ሥርዓቶችን መዘርጋት መሠረታዊ ነገር ነው። ምንጭ፡- በትምራን በተዘጋጀ የሴቶች የሰላም ፎረም ላይ ተሳታፊ የነበሩ በአማራ ክልል የሚገኙ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የጋራ የአቋም መግለጫ፣ መስከረም 2018

Read More »
Updates

The NAP aims to foster sustainable peace by empowering women across the country

ረቂቅ ብሔራዊ የሴቶች ሰላም እና ደኅንነት የድርጊት መርሐ ግብር አካባቢያዊ ተጨባጭ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ ዓለም አቀፍ የሴቶች፣ ሰላም እና ደህንነት አጀንዳዎችን ወደ ሀገራዊ ፖሊሲ በመቀየር ሴቶች በሰላም ግንባታ ሂደቶች ውስጥ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እና የውሳኔ ሰጪነት ሚና እንዲኖራቸው፣ በግጭት ወቅት መብታቸው እንዳይጣስ እንዲሁም አካታች የሆነ የሰላም ግንባታ ሂደት እንዲኖር ያደርጋል። ይህ የድርጊት መርሃ-ግብር የተረቀቀው ከመንግስት እስከ ሲቪል ማህበረሰቡ ባሉ ወገኖች ምክክር ነው። ዓላማውም በመላ ሀገሪቱ ያሉ ሴቶችን አቅም በማጠናከር እና ደህንነት በማስጠበቅ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ ነው። The Ethiopian Draft National

Read More »
Updates

WPS agenda is a global framework that empowers women as essential agents of peace and security

የሴቶች፣ ሰላምና ደኅንነት (WPS) አጀንዳ ሴቶችን እንደ ዋና የሰላምና ደህንነት ተዋናዮች የሚያበረታታ ዓለም አቀፍ መዋቅር ነው። የዚህ አጀንዳ አራቱ ምሰሶዎች ተሳትፎ፣ ጥበቃ፣ መከላከል ፣ እገዛ እና መልሶ ማቋቋም የሴቶች ድምጽ በሁሉም ሰላምና ደኅንነት ስራዎች ውስጥ መካተታቸውን  የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎች እንዲኖሩ ያደርጋሉ። The Women, Peace & Security (WPS) agenda is a global framework that empowers women as essential agents of peace and security. The agenda’s four pillars, participation, protection, prevention, and relief & recovery, guide policies and actions to ensure women’s voices

Read More »
Updates

ጠበቃ መሠረት አያሌው የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

ጠበቃ ተስፋዬ ደረሰ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነዋል የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበርን ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በአመራርነት ለማገልገል ዛሬ ታኅሣሥ 04 ቀን 2018 ዓ.ም በግራንድ ኤልያና ሆቴል በተካሄደ የምርጫ ሥነ ሥርዓት ጠበቃ መሠረት አያሌው ማኅበሩን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።በተመሳሳይ ማበኅበሩን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የሚያገለግሉ አባላት ለመሰየም በተካሄደው ምርጫ ጠበቃ ጀሚላ ክብረት እና ጠበቃ ቤዛ ንጉሤ ሴት ተወካዮች ሆነው ተመርጠዋል። ትምራን ለሦስቱ ሴት ጠበቆች እንዲሁም ማኅበሩን በአመራርነት ለማገልገል ለተመረጡት ጠበቆች በሙሉ የተሳካ የሓላፊነት ጊዜ እንዲሆንላቸው ትመኛለች።

Read More »